Get Mystery Box with random crypto!

Dirshaye (ድርሻዬ)

Logo del canale telegramma dirshayeabonehmulatu - Dirshaye (ድርሻዬ) D
Logo del canale telegramma dirshayeabonehmulatu - Dirshaye (ድርሻዬ)
Indirizzo del canale: @dirshayeabonehmulatu
Categorie: Uncategorized
Lingua: Italiano
Abbonati: 695
Descrizione dal canale

FACEBOOK: https://www.facebook.com/dirshaye https://www.instagram.com/dirshayeaboneh?r=nametag
INSTAGRAM:
TWITTER:
YOUTUBE: https://www.youtube.com/channel/UC3MYMu7t-bVzQx6v5C-7Ryg?view_as=subscriber
TIKTOK: tiktok.com/@dirshayeaboneh

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Gli ultimi messaggi

2023-04-15 21:54:02 ምግቡ መጣ…

እሷን ሳያት ምንም ነገር ማድረግ አትፈልግም።

እንጀራውን አነሳሁ። አነጣጠፍኩ። ወጡን ጨለፍኩ። ፈሰስ አደረግኩ። ግማሽ በእኔ በኩሉ ግማሽ በእሷ በኩል። እሷ ታየኛለች። ፓስታውን ቆራረጥኩት። ከጎን አደረግኩ። በእሷ በኩልም አደረግኩላት። ጎመኑን አደረግኩ። ሚጥሚጣ ለእኔም ለእሷም አደረግኩኝ። አታየኝም ሁሉ።

ይቺ ልጅ ትበላ ይሆን?… ውሃ ቀዳሁ።

አጎረስኳት።

«አይጣፍጥም» አለች።

«ምን ሆነብሽ?»

«እኔ እንጃ ምን እንደሆነ አላወቅኩም ብቻ ግን አይጣፍጥም።»

ቀመስኩት። ጨው ነሰነስኩበት። አጎረስኳት።

«አሁን ይጣፍጣል» አላለችም

ይቺማ ማድቤት ገብታ አታውቅም። በረሃብ ነው የምትገለኝ። አምልጥ ብራዘር

#first_date_ላይ_እንኳን_ኢምፕረስ_አርጉነ
#የእናቷን_ዶሮ_እያማሰለች_ስቶሪ_ለጥፋ_ሸወደችኝ

@dirshayeabonehmulatu
155 views18:54
Aprire / Come
2023-04-11 00:24:54 ከእንቅልፌ ስነቃ ጭንቅላቴ ውስጥ የምትመላለሽው አንቺ ነሽ። ልተኛ ስልም የማስበው አንቺን ነው። ስላንቺ ማሰብ ስራዬ ነው። አንቺን እንዳላስብ ካናጠበኝ ስራዬ የማርፈውም አንቺኑ እያሰብኩ ነው። አርፌ አላውቅም ማለት ነው?

አንደኛውን ልቤን ሰብረሽው በነበረ ብዬ እመኛለሁ… ቀስ ብዬ እድን ነበር።

ጥሩ ሰው ባትሆኝልኝ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ። አስቀይመሽኝ ሄደሽ ቢሆን ብዬ እመኛለሁ… እጠላሽ ነበር። በጥላቻዬ ውስጥ ፍቅሬን አዳፍን ነበር።

አብረን ብንሆን ኖሮ ምን አይነት ግንኙነት ይኖረን ነበር ብዬ ባላስብ እመኛለሁ። ልቤን ሰብረሽው ሄደሽ ቢሆንስ እንዴት turn out ያደርግ ነበር ብዬ ባላስብ እመኛለሁ።

ስለኔ ሚሰማሽን ከመናገር ይልቅ ዝምታን ባትመርጪ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ። ትንሽ ጊዜ ቢሆንም አብረሽኝ ሆነሽ በነበር ብዬ እመኛለሁ።

አንዴ እንኳን አብረሽኝ ሳትሆኚ፣ ለእኔ ያለሽን ፍቅር ሰጥተሽኝ ሳታውቂ፣ እወድሃለሁ እንኳን ብለሽኝ ሳታውቂ፣ የሴት መለኪያ ጣሪያዬን ከፍ አደረግሽው።

ከእኔ ጋር ማርጀት እንደምትፈልጊ እንደነበር ይሰማኛል። እቅድ እንደነበረሽ ይሰማኛል። የሆነ የሆነ ነገሬ ደስ እንደሚልሽ እንደነበር ይሰማኛል። ደስ ሲለኝ ደስ እንደሚልሽ እንደነበር ይሰማኛል። እንደምትፀልዪልኝ እንደነበር ይሰማኛል። ከራስሽ እንደምታስበልጪኝ እንደነበር ይሰማኛል። በጣም እንደምትወጂኝ እንደነበረ ይሰማኛል።

ግን ከይሰማኛል አልፌ ባውቅ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ።

አውቃለሁ። ለእኔ ጥሩውን እንደምትመኚልኝ አውቃለሁ። ልትጎጂኝ እንዳልፈለግሽ አውቃለሁ። እኔ ስሄድ ምን ይሆናል ብለሽ ፍቅርሽን በውስጥሽ አፍነሽው እንደቀረሽ አውቃለሁ። የማላስጨርሰውን አላስጀምረውም ብለሽ ዝም እንዳልሽኝ አውቃለሁ። ሳቅሽን እንደምወደው ስለምታውቂ ከህመምሽ ጋር እየታገለሽ ፈገግ እንደምትዪልኝ እንደነበር አውቃለሁ።

We weren't even together… but Moving on from you will be the hardest thing that i'll ever have to do in my entire life.

ቻው ብለሽኝ፣ ተሰናብተሽኝ ቢሆን ኖሮ ብዬ እመኛለሁ።

አንቺን አለማሰብ መቻል በህይወቴ ላደርጋቸው ከምሞክራቸው ነገሮች ውስጥ ከባዱ ነገር ነው።

ልረሳሽ እመኛለሁ።

@dirshayeabonehmulatu
193 viewsedited  21:24
Aprire / Come
2023-04-11 00:24:35 የረፈደ #motivationforሰኞ

ልክ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን ምን ይደብረኛል መሰለህ… «መጀመር ከፈለግክ አሁኑኑ ጀምር። ዛሬውኑ። ነገ አትበል… ጊዜው አሁን ነው… » ምናምን የሚሉት ስብከት። አይጥመኝም።

አንድ ነገር ለመጀመር የሆነ መስመር ሲኖር ደስ ይላል። አዲስ የምትሞክርበት ነገር ስታገኝ ለመሞከር ትነሳሳለህ።

ልጅ እያለን አዲስ ገፅ ስንገልጥ ፅሁፋችንን ለማሳመር እንደምንሞክረው ማለት ነው። ከዛ ትንሽ እንደፃፍን ማሳመሩን ረስተነው እንደበፊቱ መፃፍ እንጀምራለን። ከዛ ደሞ አዲስ ገፅ ስንገባ እንደ አዲስ እንሞክራለን። ሊሳካም ላይሳካም ይችላል… ሁሌ በየአዲሱ ገፅ ከሞከርን ግን መሳካቱ የማይቀር ነገር ነው።

ዛሬ ሰኞ ነው። … የሳምንቱ አዲስ መስመር… ተንቦራጨቅበት ብሮውውው…

አልሳካ ካለህ ደግሞ ቀጣይ ሰኞ እንደ አዲስ ትሞክራለህ… አለቀ በቃ።

(እኔማ tiktok ከፍቼ ማነቃቃት ልጀምር መሰለኝ)

@dirshayeabonehmulatu
147 views21:24
Aprire / Come
2023-04-02 20:57:12 ዜግነት፣ ብሄር፣ ሚስት እና ሃይማኖት ሳይቀር በሚቀየርበት ሃገር ውስጥ ከፈጣሪ የታዘዘልኝ ክለብ ይመስል የማንቺስተር ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ ብዬ ችክ ማለት ያለብኝ አይመስለኝም።

በዚህ ሰዓት የአርሰናል ደጋፊ ሆኜ ደስተኛ የሆኑ ኑሮ መምራት ነው ምፈልገው
217 views17:57
Aprire / Come
2023-04-01 07:43:59 እንደምን አደራችሁ ወዳጆቼ
(ድርሻዬ አቦነህ)

ደግ ናችሁ ወይ?… እኔ በጣም ደህና ነኝ። እናንተን ግን ደብሯችሁ ወይም ከፍቷችሁ ከሆነ ላፅናናችሁ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእናንተ እኩል VPN connect አድርጎ እንደሚፖስት ታውቃላችሁ? ad ምናምን ይመጣበትና ይበሳጫል ሁሉ። የቴሌዋ ፍሬህይወትም እንደዛው። ልዩነቱ እነሱ ፈልገውት እኛ ግን ተገደን መሆኑ ነው።

በጣም የሚገርምም የሚያስቅም ነገር ነው… በዘጉት social media ላይ ለማን መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሚፖስቱ አላውቅም። ወደ ታች ስናመጣው… እድሩ እንዳይሰበሰብ የከለከሉት የእድሩ ሰብሳቢ፣ እሁድ ጠዋት ወደ እድር መሰብሰቢያ አዳራሽ ገብተው፣ መድረክ ላይ ወጥተው፣ የእድሩ አባላት በሌሉበት መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደማለት ነው።

በእርግጥ ፈልገውት ሳይሆን እምቢ ብሏቸው ነው የሚል አለ። @ethio_telecom እምቢ ብሏችሁ ነው ወይ? ከሆነ ንገሩን። እግዚአብሔርን ንገሩን። እንኳን ይሄንን ስንት ችግር ተረድተን ችለን የኖርን ሰዎች ነን። ለማስተካከል እየሞክርን ነው ምናምን ምናምን በሉንኮ… በቃ ያራዳ ልጅ ጣጣ የለውም ብለን ላሽ እንላለን።

የምርም እምቢ ብሏችሁ ከሆነ ግን የነዋይ ደበበን ዘፈን አያይዛችሁ በዛውም ለህዝቡ ማፍረስ ቀላል ነገር መስራት ደሞ ከባድ ነገር እንደሆነ በMotivational speech መልክ ብትሰጡልኝ ደስ ይለኛል።

«ቢያወሩት ምን ሊበጅ ሆድ ይፍጀው ሆድ ይፍጀው…
ቃል ነበረ ክብሩ ሁሌም ማያረጀው
መገንባት ነው እንጂ ደቦ ሚያስፈልገው
አንቺው ትበቂያለሽ ሲፈርስ አትጥሪ ሰው
ሲፈርስ አትጥሪ ሰው።»

ስራውን ፌስቡክ ላይ boost አድርጎ በማስተዋወቅ ይሰራ የነበረ አንድ ጓደኛዬ ስራ እንዴት ነው ስለው… «ምን ባክህ እኛ እንፖስታለን ፈረንሳይ እና ካናዳ ያሉ ሰዎች ናቸው የሚያዩት» ብሎኛል።

«ታዲያ ለምን export አትጀምርም?» አልኩት።

«ዕቃው ለውጭ ሃገር የሚሆን አይደለም»

«ምንድነው የምትሸጠው?»

«ምጣድ ማሟሻ ጎመን ዘር»

ጎመን ዘር ለመሸጥ ከፌስቡክ ad ይልቅ እናቶች የሚገኙበት እድር ስብሰባ ላይ እየዞረ ቢሞክር የበለጠ እንደሚያዋጣው የሚያስረዳ የ10 ደቂቃ አነቃቂ ምክር ለቀቅኩበት።

@dirshayeabonehmulatu
214 views04:43
Aprire / Come
2023-03-31 12:18:09 ሳላውቅሽ ጀምሮ ነው የምትናፍቂኝ።

ማውራት ከጀመርን ቀን ጀምሮ ትናፍቂኛለሽ። እንድንገናኝ ለማድረግ ስሞክር ትናፍቂኛለሽ። ስጀነጅንሽ፣ hard to get ስትጫወቺ ትናፍቂኛለሽ። ስልክ አላነሳ ስትዪኝ ትናፍቂኛለሽ። ቀጥረሺኝ ስትቀሪ ትናፍቂኛለሽ…

በእርግጥ መናፈቄን እወደዋለሁ። ደስ የሚል ስቃይ የሚሉት አይነት ነገር ነው።

ለናፍቆቴ ምላሽ ሳትሰጪ ስትቀሪ ደግሞ ይብስብኛል… እብሰለሰላለሁ… ናፍቆቴ እጅጉን ይጨምራል። ካንቺ ውጪ ማንም እንዲህ ናፍቆኝ አያውቅም ብልሽ ላታምኚኝ ትችያለሽ። ካንቺ ውጪም ማንም መናፈቄን ችላ ብሎብኝ አያውቅምም ነበር።

ታውቂያለሽ…?… የማያውቁት ሃገር አይናፍቅም የሚሉት ውሸት እንደሆነ?… ታዲያ እውነት ቢሆን የት አውቄሽ ትናፍቂኝ ነበር? በአካል እንኳን አግኝቼሽ ሳላውቅ? የሳልኳት አንቺ ነሽ የምትናፍቂኝ?

እንደሳልኳት እንዳሰብኳት ባትሆንስ ብሎ እንኳን ልቤ አላመነታም… በመውደዱ በመናፈቁ ቀጠለ። ምን ይደረግ… እኔ አልቆጣጠረው…

እየለመድሽኝ እና እየለመድኩሽ ስትመጪ የበለጠ ትናፍቂኛለሽ። ስንግባባ የበለጠ ትናፍቂኛለሽ። Chat እያደረግን ትናፍቂኛለሽ። ስልክ ስናወራ ትናፍቂኛለሽ።

በመጨረሻም ተገናኘን። አሁን ናፍቆቴ ሊወጣለኝ… ጋብ ሊልልኝ ነው መሰለኝ…?።

ግን ችግሩ ምን መሰለሽ ውዴ…? ብዙ ቀን ባገኝሽም፣ ብዙ ቀን ረጅም ሰዓቶችን አብረን ብናሳላፍም፣ ለመውደዴ ምላሽ እኔም እወድሃለሁ ብትዪኝም፣ ገላሽን ብጋራሽም፣ ራቆትሽን ባይሽም…

ተገናኝተን ልክ ስንለያይ አሁንም እንደቀደመው ትናፍቂኛለሽ። ቻው ብዬ ከንፈርሽን በሳምኩሽ ቅፅበት ካንቺ ውጪ አላስብም።

ለነገሩ ይጋነናል ብዬ ነው እንጂ… ማንም አያምነኝም ብዬ ነው እንጄ… ባክህ እንዲህ አይነት ፍቅር የለም ብለው ይስቁብኛል ይሳለቁብኛል ብዬ ነው እንጂ…

አብረን ቁጭ ብለንም ትናፍቂኛለሽ። አቅፌሽም ትናፍቂኛለሽ። እየሳምኩሽም ትናፍቂኛለሽ።

አሁንም ናፍቀሽኛል!

@dirshayeabonehmulatu
179 views09:18
Aprire / Come
2023-03-21 06:57:04 በፌስቡክ ተዋወቁ። ላይክ ተደራረጉ። ኮመንት ተደራረጉ። ትንሽ አወሩ። ተማሪ ወይስ ሰራተኛ አላት። ተማሪ እንደሆነች ነገረችው፣ ሰራተኛ እንደሆነ ነገራት።

ቴሌግራም ትጠቀሚያለሽ ወይ አላት። አዎ አለችው። የወሬ ሜዳ ቀየሩ። በደንብ አወሩ። በደንብ ተግባቡ። ሳያወሩ አያድሩም። ተደዋወሉ። አንተ ዝጋው አንቺ ዝጊው ተባባሉ።

ሊገናኙ ተስማሙ። ተገናኙ። ማኪያቶ ጠጡ። ምሳ በሉ። ደጋገሙት። ወደዱት። ተንከባከባት። በደንብ ተንከባከባት። እራት በሉ። ሳማት። እወድሻለሁ አላት። እኔም ወድጄሃለሁ አለችው።

ቤቱ ሄደች። ቤቱን አስተካከለችለት። ምግብ ሰራችለት። ቡና አፈላችለት። ደስ አለው።

አብረው ዋሉ። አብረው አደሩ። ደጋገሙት። ወደዱት። ደስ አላቸው። ደጋግመው አብረው አደሩ። ደጋግመው ደስ አላቸው። አሁንም ወደዱት።

።።።።።።።።።።።
አረገዘች። ፕሮፖዝ አደረጋት። ሽማግሌ ላከ። ቀለበት አደረገላት።

ተጋቡ።

ልጅ ወለዱ።

ጊዜው ሄደ። ሰለቸችው። ሰለቻት። አንደኛው ሰው የማይወደውን ነገር አንደኛው ማድረግ ጀመረ። ተጣሉ። ፀብ በዛ። ለልጃቸው ሲሉ አብረው ለመኖር ተስማሙ። ትንሽ ቆዩ። አልቻሉም። ፀብ በዛ። ፀብ። ፀብ። ፀብ። ተጣሉ።

ተፋቱ።

ልጄን አምጪ። ልጄን አምጣ ተባባሉ። ተካሰሱ። ዳኛ ፊት ቆሙ።
።።።።።።።።።።
ወይም
።።።።።።።።።።
አረገዘች። ካደ። ተጣሉ። ያንተ ልጅ ነው አለችው። አስወርጂው አላት። እሷም ያለ አባት ማሳደጉን ፈራች።

አስወረደችው።

አብረው ቆዩ። እንደመጀመሪያው ለመቀጠል ሞከሩ። ቀጠሉ። ደጋገሙት። ሰለቸው። ሌላ ሴት ደረበባት። አወቀችበት። ይቅርታ ጠየቃት። ይቅርታ አደረገችለት። አብረው ቆዩ። ተሰላቹ። እንደበፊቱ አልሆኑም። ፀብ በዛ።

ተለያዩ።
።።።።።።።።።።
ወይም
።።።።።።።።።።
አረገዘች። ካደ። ተጣሉ። ያንተ ልጅ ነው አለችው። አስወርጂው አላት። አላስወርድም አለች። ጉዳይሽ አላት።

ወለደችው።

ተቆራጭ አምጣ ብላ ከሰሰቸው። በወር የሆነ ያህል ብር ተቆራጭ እንዲሰጥ ተፈረደበት። ሌላ ሴት ተዋወቀ። ህይወት ቀጠለ።

ከአመታት በኋላ መጣ። አባት መሆን ፈለገ። ልጄን ስጪኝ አላት። እምቢ አለች። ከሰሳት።
።።።።።።።።።።
ወይም
።።።።።።።።።
አረገዘች። (ለምን ከዚህ ሁሉ ኮንዶም አይጠቀሙም?)…

ወደ ኋላ እንመለስ።

ቤቱ ሄደች። ቤቱን አስተካከለችለት። ምግብ ሰራችለት። ቡና አፈላችለት። ደስ አለው።

አብረው አደሩ። ደጋገሙት። ወደዱት። ደስ አላቸው። ደጋግመው አብረው አደሩ። ደጋግመው ደስ አላቸው። አሁንም ወደዱት። ፍቅራቸው ጨመረ። በጣም ተዋደዱ። ሳያስቡት አብረው መኖር ጀመሩ።

የሆነ ቀን ጓደኞቿን ሰበሰበ። ጓደኞቹን ጠራ። ሰርፕራይዝ አላት። ፕሮፖዝ አደረጋት። ታገቢኛለሽ ወይ አላት። እሺ አለችው።

ሽማግሌ ላከ። ቀውጢ ሰርግ ተደገሰ። ዘመድ አዝማድ ተጠራ። ተበላ ተጠጣ። ተጨፈረ።

አናስገባም ሰርገኛ፣ ሙሽራዬ፣ አትሸኟትም ወይ ተባለ።

ተጋቡ።

ልጅ ሞከሩ። እምቢ አላቸው። ሞከሩ እምቢ አላቸው።

ተፋቱ።
።።።።።።።።።።

@dirshayeabonehmulatu
219 views03:57
Aprire / Come
2023-03-20 07:19:23 ATM ማሽኑ ጋር ግርግር ነገር አይቼ እንደማንኛውም የአዲስአበባ ነዋሪ ወሬ ለማየት ተጠጋሁ።

«ዝርዝር ብር ለምንድነው የማታስገቡት?» ይላል አንደኛው ሰውዬ በቁጣ። የባንኩ ሰራተኛ መለሰ። «ዝርዝር ብር ለጊዜው ስለሌለን ነው… ሲኖረን እናስገባለን አካውንት አለህ እኛ ብራንች?»… «አዎ አለኝ። የሰራሁትን እዚህ ባንክ ነው የማስቀምጠው። የበፊቱ ማናጀር እያለ ዝርዝር ሲያልቅ ወዲያው ታስገቡ ነበር። አሁን ይሄ አሰራር የለም። ልክ አይደለም የምትሰሩት ስራ።» ቁጣው ፊቱ ላይ ይነበባል።

«እናስተካክላለን ATM ወስደዋል?»… ባንከሩ ሌላ ጥያቄ ጠየቀ። «አልወሰድኩም። እኛ ATM ውስጥ ዝርዝር ባለመኖሩ የተነሳ ስራችንን በአግባቡ ሰርተን ራሳችንን እና ቤተሰባችንን ማስተዳደር አልቻልንም። ጉዳዩ በጣም ትኩረት ይፈልጋል። እንደቀልድ አትዩት… በጣም ተደጋገመ»

ትንሽ ግርርር ስላለኝ እና ወሬ ስለምወድ በደንብ ለማጣራት ብዬ ጣልቃ ገባሁ።

«የኔ ወንድም ለስራህ ዝርዝር ብር በጣም ያስፈልግሃል ማለት ነው?» ብዬ ሰውዬውን መጠየቅ። (የታክሲ ረዳት ደሞ አይመስልም)

«አዎ ATM ውስጥ ዝርዝር ከሌለ ማግኘት ያለብኝን ገቢ ያህል አላገኝም»

"ምንድነው የምትሰራው?»… ኮራ ብሎ በፍጥነት መለሰልኝ… «ልመና»

በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ መብታችሁን አስከብሩ ለማለት ነው … ደህና ዋሉ።

#motivationforሰኞ

@dirshayeabonehmulatu
172 views04:19
Aprire / Come
2023-03-18 21:16:14
የሃገር ባህል ልብስ ብለው ነው የሰፉለት አሉ

@dirshayeabonehmulatu
180 viewsedited  18:16
Aprire / Come
2023-03-18 12:33:23 የእናቶች ወግ የሚለው ግሩፕ ውስጥ አንደኛዋ እናት «ለባላችሁ የላካችሁት የመጨረሻ txt ምን ይላል?» ብላ ጠየቀች።

መልሶቹን ኮመንት ውስጥ ገብቼ አነበብኩኝ። almost ሁሉም ማለት ይቻላል ዳቦ ይዘህ ና ነው የሚሉት።

ዳቦ እንዳትረሳ፣ ዳቦ ግዛ፣ ዳቦ ከልያዝክ እዛው ቅር፣ ዳቦ አልቋል፣ ዳቦውን ከዛኛው ሱቅ እንዳትገዛ ሰፈር ካለው ግዛ፣ ዳቦ ካላመጣህ ምግብ የለም፣ ዳቦ ካላመጣህ ዳቦ የለም (ይቺኛዋ ቢያንስ ታስቀዋለች)፣ ዳቦውን እንዳታሳንሰው፣ የገብስ ዳቦም ጨምርበት… ወዘተ

መጀመሪያ ያሰብኩት… ዳቦ በዚህ ደረጃ የምንበላ ከሆነ የጤፍ መወደድ ይሄን ያህል ለምን ያሳስበናል የሚለው ነበር። ወዲያው ግን ደንገጥ ብዬ ከፍቅረኛዬ ጋር የምላላከውን sms ከፈትኩት። የመጨረሻውን txt የላከችው እሷ ነች። እንዲህ ይላል…

«መልካም ቀን ይሁንልህ የኔ ፍቅር… የኔ ስለሆንክ እድለኛ ነኝ። ስላንተ እያሰብኩኝ እንደምውል አስታውስ። በየደቂቃው ትናፍቀኛለህ። ደሞ ብርድ ነው ጃኬት ወይም ሹራብ መያዝህን እንዳትረሳ ትታመምብኛለህ… እወድሃለሁ።»

ይሄ txt ነው እንግዲህ… «ዳቦ ካልያዝክ ወደ ቤት ዝር እንዳትል» ወደሚል የተቀየረው።

ከዛ ትዳር ፈራሁ… … ለትንሽ ሰዓት መጨናነቄ አልቀረም… ባል ነኝ ወይስ ተላላኪ ምናምን ብዬ ብዙ አሰብኩኝ። እራሷ አትገዛም እንዴ ምናባቷ… ብዬ ያላገባኋት ሚስቴ ላይ ተነጫነጭኩኝ።

መልሼ ወደ ላይ ወጥቼ ብዙ txt አነበብኩኝ… ይቺ ልጅ ትወደኝ የለ እንዴ በስማም… የሆነ ቀን ድንገት ተነስታ "ዳቦ አምጣ" ብላማ አታስደነግጠኝም።

ይሄንን ነገር ለማቆየት ምን ማድረግ አለብን?… ጥቂት ካሰብኩኝ በኋላ ገባኝ። ለካ በጣም ቀላል ነው። ጥፋቱ የባሎች ነው። ዳቦውን ባል ራሱ አስታውሶ ቢገዛ በማግስቱ ጣፋጭ የፍቅር መልዕክት እንደሚደርሰው እርግጠኛ ነኝ።

a friend asking me a question: «ለሚስትህ ምን አይነት ባል መሆን ትፈልጋለህ?»…

እኔ: «ዳቦ ራሱ አስታውሶ የሚገዛ ባል»

a rich friend interrupting: ዳቦ ቤት ከፍተህላት መገላገል ነዋ…

@dirshayeabonehmulatu
182 views09:33
Aprire / Come