Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን አደራችሁ ወዳጆቼ (ድርሻዬ አቦነህ) ደግ ናችሁ ወይ?… እኔ በጣም ደህና ነኝ። እናንተን | Dirshaye (ድርሻዬ)

እንደምን አደራችሁ ወዳጆቼ
(ድርሻዬ አቦነህ)

ደግ ናችሁ ወይ?… እኔ በጣም ደህና ነኝ። እናንተን ግን ደብሯችሁ ወይም ከፍቷችሁ ከሆነ ላፅናናችሁ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእናንተ እኩል VPN connect አድርጎ እንደሚፖስት ታውቃላችሁ? ad ምናምን ይመጣበትና ይበሳጫል ሁሉ። የቴሌዋ ፍሬህይወትም እንደዛው። ልዩነቱ እነሱ ፈልገውት እኛ ግን ተገደን መሆኑ ነው።

በጣም የሚገርምም የሚያስቅም ነገር ነው… በዘጉት social media ላይ ለማን መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሚፖስቱ አላውቅም። ወደ ታች ስናመጣው… እድሩ እንዳይሰበሰብ የከለከሉት የእድሩ ሰብሳቢ፣ እሁድ ጠዋት ወደ እድር መሰብሰቢያ አዳራሽ ገብተው፣ መድረክ ላይ ወጥተው፣ የእድሩ አባላት በሌሉበት መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደማለት ነው።

በእርግጥ ፈልገውት ሳይሆን እምቢ ብሏቸው ነው የሚል አለ። @ethio_telecom እምቢ ብሏችሁ ነው ወይ? ከሆነ ንገሩን። እግዚአብሔርን ንገሩን። እንኳን ይሄንን ስንት ችግር ተረድተን ችለን የኖርን ሰዎች ነን። ለማስተካከል እየሞክርን ነው ምናምን ምናምን በሉንኮ… በቃ ያራዳ ልጅ ጣጣ የለውም ብለን ላሽ እንላለን።

የምርም እምቢ ብሏችሁ ከሆነ ግን የነዋይ ደበበን ዘፈን አያይዛችሁ በዛውም ለህዝቡ ማፍረስ ቀላል ነገር መስራት ደሞ ከባድ ነገር እንደሆነ በMotivational speech መልክ ብትሰጡልኝ ደስ ይለኛል።

«ቢያወሩት ምን ሊበጅ ሆድ ይፍጀው ሆድ ይፍጀው…
ቃል ነበረ ክብሩ ሁሌም ማያረጀው
መገንባት ነው እንጂ ደቦ ሚያስፈልገው
አንቺው ትበቂያለሽ ሲፈርስ አትጥሪ ሰው
ሲፈርስ አትጥሪ ሰው።»

ስራውን ፌስቡክ ላይ boost አድርጎ በማስተዋወቅ ይሰራ የነበረ አንድ ጓደኛዬ ስራ እንዴት ነው ስለው… «ምን ባክህ እኛ እንፖስታለን ፈረንሳይ እና ካናዳ ያሉ ሰዎች ናቸው የሚያዩት» ብሎኛል።

«ታዲያ ለምን export አትጀምርም?» አልኩት።

«ዕቃው ለውጭ ሃገር የሚሆን አይደለም»

«ምንድነው የምትሸጠው?»

«ምጣድ ማሟሻ ጎመን ዘር»

ጎመን ዘር ለመሸጥ ከፌስቡክ ad ይልቅ እናቶች የሚገኙበት እድር ስብሰባ ላይ እየዞረ ቢሞክር የበለጠ እንደሚያዋጣው የሚያስረዳ የ10 ደቂቃ አነቃቂ ምክር ለቀቅኩበት።

@dirshayeabonehmulatu