Get Mystery Box with random crypto!

የረፈደ #motivationforሰኞ ልክ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን ምን ይደብረኛል መሰለህ… | Dirshaye (ድርሻዬ)

የረፈደ #motivationforሰኞ

ልክ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን ምን ይደብረኛል መሰለህ… «መጀመር ከፈለግክ አሁኑኑ ጀምር። ዛሬውኑ። ነገ አትበል… ጊዜው አሁን ነው… » ምናምን የሚሉት ስብከት። አይጥመኝም።

አንድ ነገር ለመጀመር የሆነ መስመር ሲኖር ደስ ይላል። አዲስ የምትሞክርበት ነገር ስታገኝ ለመሞከር ትነሳሳለህ።

ልጅ እያለን አዲስ ገፅ ስንገልጥ ፅሁፋችንን ለማሳመር እንደምንሞክረው ማለት ነው። ከዛ ትንሽ እንደፃፍን ማሳመሩን ረስተነው እንደበፊቱ መፃፍ እንጀምራለን። ከዛ ደሞ አዲስ ገፅ ስንገባ እንደ አዲስ እንሞክራለን። ሊሳካም ላይሳካም ይችላል… ሁሌ በየአዲሱ ገፅ ከሞከርን ግን መሳካቱ የማይቀር ነገር ነው።

ዛሬ ሰኞ ነው። … የሳምንቱ አዲስ መስመር… ተንቦራጨቅበት ብሮውውው…

አልሳካ ካለህ ደግሞ ቀጣይ ሰኞ እንደ አዲስ ትሞክራለህ… አለቀ በቃ።

(እኔማ tiktok ከፍቼ ማነቃቃት ልጀምር መሰለኝ)

@dirshayeabonehmulatu