Get Mystery Box with random crypto!

ከእንቅልፌ ስነቃ ጭንቅላቴ ውስጥ የምትመላለሽው አንቺ ነሽ። ልተኛ ስልም የማስበው አንቺን ነው። ስ | Dirshaye (ድርሻዬ)

ከእንቅልፌ ስነቃ ጭንቅላቴ ውስጥ የምትመላለሽው አንቺ ነሽ። ልተኛ ስልም የማስበው አንቺን ነው። ስላንቺ ማሰብ ስራዬ ነው። አንቺን እንዳላስብ ካናጠበኝ ስራዬ የማርፈውም አንቺኑ እያሰብኩ ነው። አርፌ አላውቅም ማለት ነው?

አንደኛውን ልቤን ሰብረሽው በነበረ ብዬ እመኛለሁ… ቀስ ብዬ እድን ነበር።

ጥሩ ሰው ባትሆኝልኝ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ። አስቀይመሽኝ ሄደሽ ቢሆን ብዬ እመኛለሁ… እጠላሽ ነበር። በጥላቻዬ ውስጥ ፍቅሬን አዳፍን ነበር።

አብረን ብንሆን ኖሮ ምን አይነት ግንኙነት ይኖረን ነበር ብዬ ባላስብ እመኛለሁ። ልቤን ሰብረሽው ሄደሽ ቢሆንስ እንዴት turn out ያደርግ ነበር ብዬ ባላስብ እመኛለሁ።

ስለኔ ሚሰማሽን ከመናገር ይልቅ ዝምታን ባትመርጪ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ። ትንሽ ጊዜ ቢሆንም አብረሽኝ ሆነሽ በነበር ብዬ እመኛለሁ።

አንዴ እንኳን አብረሽኝ ሳትሆኚ፣ ለእኔ ያለሽን ፍቅር ሰጥተሽኝ ሳታውቂ፣ እወድሃለሁ እንኳን ብለሽኝ ሳታውቂ፣ የሴት መለኪያ ጣሪያዬን ከፍ አደረግሽው።

ከእኔ ጋር ማርጀት እንደምትፈልጊ እንደነበር ይሰማኛል። እቅድ እንደነበረሽ ይሰማኛል። የሆነ የሆነ ነገሬ ደስ እንደሚልሽ እንደነበር ይሰማኛል። ደስ ሲለኝ ደስ እንደሚልሽ እንደነበር ይሰማኛል። እንደምትፀልዪልኝ እንደነበር ይሰማኛል። ከራስሽ እንደምታስበልጪኝ እንደነበር ይሰማኛል። በጣም እንደምትወጂኝ እንደነበረ ይሰማኛል።

ግን ከይሰማኛል አልፌ ባውቅ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ።

አውቃለሁ። ለእኔ ጥሩውን እንደምትመኚልኝ አውቃለሁ። ልትጎጂኝ እንዳልፈለግሽ አውቃለሁ። እኔ ስሄድ ምን ይሆናል ብለሽ ፍቅርሽን በውስጥሽ አፍነሽው እንደቀረሽ አውቃለሁ። የማላስጨርሰውን አላስጀምረውም ብለሽ ዝም እንዳልሽኝ አውቃለሁ። ሳቅሽን እንደምወደው ስለምታውቂ ከህመምሽ ጋር እየታገለሽ ፈገግ እንደምትዪልኝ እንደነበር አውቃለሁ።

We weren't even together… but Moving on from you will be the hardest thing that i'll ever have to do in my entire life.

ቻው ብለሽኝ፣ ተሰናብተሽኝ ቢሆን ኖሮ ብዬ እመኛለሁ።

አንቺን አለማሰብ መቻል በህይወቴ ላደርጋቸው ከምሞክራቸው ነገሮች ውስጥ ከባዱ ነገር ነው።

ልረሳሽ እመኛለሁ።

@dirshayeabonehmulatu