Get Mystery Box with random crypto!

ATM ማሽኑ ጋር ግርግር ነገር አይቼ እንደማንኛውም የአዲስአበባ ነዋሪ ወሬ ለማየት ተጠጋሁ። «ዝ | Dirshaye (ድርሻዬ)

ATM ማሽኑ ጋር ግርግር ነገር አይቼ እንደማንኛውም የአዲስአበባ ነዋሪ ወሬ ለማየት ተጠጋሁ።

«ዝርዝር ብር ለምንድነው የማታስገቡት?» ይላል አንደኛው ሰውዬ በቁጣ። የባንኩ ሰራተኛ መለሰ። «ዝርዝር ብር ለጊዜው ስለሌለን ነው… ሲኖረን እናስገባለን አካውንት አለህ እኛ ብራንች?»… «አዎ አለኝ። የሰራሁትን እዚህ ባንክ ነው የማስቀምጠው። የበፊቱ ማናጀር እያለ ዝርዝር ሲያልቅ ወዲያው ታስገቡ ነበር። አሁን ይሄ አሰራር የለም። ልክ አይደለም የምትሰሩት ስራ።» ቁጣው ፊቱ ላይ ይነበባል።

«እናስተካክላለን ATM ወስደዋል?»… ባንከሩ ሌላ ጥያቄ ጠየቀ። «አልወሰድኩም። እኛ ATM ውስጥ ዝርዝር ባለመኖሩ የተነሳ ስራችንን በአግባቡ ሰርተን ራሳችንን እና ቤተሰባችንን ማስተዳደር አልቻልንም። ጉዳዩ በጣም ትኩረት ይፈልጋል። እንደቀልድ አትዩት… በጣም ተደጋገመ»

ትንሽ ግርርር ስላለኝ እና ወሬ ስለምወድ በደንብ ለማጣራት ብዬ ጣልቃ ገባሁ።

«የኔ ወንድም ለስራህ ዝርዝር ብር በጣም ያስፈልግሃል ማለት ነው?» ብዬ ሰውዬውን መጠየቅ። (የታክሲ ረዳት ደሞ አይመስልም)

«አዎ ATM ውስጥ ዝርዝር ከሌለ ማግኘት ያለብኝን ገቢ ያህል አላገኝም»

"ምንድነው የምትሰራው?»… ኮራ ብሎ በፍጥነት መለሰልኝ… «ልመና»

በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ መብታችሁን አስከብሩ ለማለት ነው … ደህና ዋሉ።

#motivationforሰኞ

@dirshayeabonehmulatu