Get Mystery Box with random crypto!

የኣማራ ክልል ባለስልጥናት በመሃካልቸው የተፈጥረው ኣለመተማመን የጠባቂዎቻቸው ቁጥር እንዲጭምሩ | Kulu Media ኩሉ ሚድያ

የኣማራ ክልል ባለስልጥናት በመሃካልቸው የተፈጥረው ኣለመተማመን የጠባቂዎቻቸው ቁጥር እንዲጭምሩ ምክንያት እየሆነ እንደሆነ ተነገረ



በደብረወርቅ ዛሬ የተካሄደው የፋኖ እናብልጽግና ሽምግልና መክሸፉ ተከትሎ የምስራቅ ጎጃም ባለስልጣን ዛሬ ከ10:00-12:00 በደብረወርቅና በመርጦ ለማርያም ባለስልጣን ደህንነት ጉዳይ ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበረ የተነገረ ሲሆን፡



የደብረወርቅና የመርጦ ለማርያም ባለስልጣናት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዳለባቸው የዞኑ ባለስልጣናት ብስብሰባው ላይ ስምምነት ላይ ከደረሱ ቡሃላ በሁለቱ ከተማዎች ባለስልጣናትን የሚጠብቅ ሁለት መቶ- ሁለት መቶ አድማ በታኝ በቋሚነት እንዲመደብ መውሰናቸው ተሰምተዋል



ከነገ ጀምሮ ይህ ሀይል በተጠቀሱት ከተሞች እንደሚሰመራ የተነገረው ሲሆን ከደብረወርቅ በተገኘ መረጃ ለዚህ ሀይል መኖሪያ ደርግ ያሰራው የእርሻ ሰብል አዳራሽ ስለሆነ ይህ አዳራሽ ነገ ጠዋት እንዲፀዳ ትዛዝ መሰጠቱም ተሰምተዋል፡


የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ባለስልጣኑ ቢሮ ሲገቡ ይህ ሀይል ቢሯቸው ሆኖ ይጠብቃቸዋል፣ ቤታቸው ሲሄዱም ቤታቸው አብሮ ሄዶ እንደሚጠብቃቸው ተሰምትዋል


የኣማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኣመራሮች እንደዚህ ኣይነት ኣጣብቂኝ ውስጥ በመግባታቸው እርስበራሳቸው ያላቸው መተማመን እና ትስስር እየላላ እንድሄድ ምክንያቱ እየሆነ መሁኑም ተነግረዋል

More info t.me/KuluMedia
ኩሉ ሚድያ
ድምፂ ሓቂ