Get Mystery Box with random crypto!

ኩዌት በወርሃዊ የ300 ዶላር ክፍያ ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ልትቀጠር መሆኑ ተገለጸ ኩዌት የሦስት | Kulu Media ኩሉ ሚድያ

ኩዌት በወርሃዊ የ300 ዶላር ክፍያ ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ልትቀጠር መሆኑ ተገለጸ

ኩዌት የሦስት ወራት አስገዳጅ ስልጠና የወስዱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተገልጿል።

በኹለቱ መንግሥታት በኩል መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎም፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጋራ የሥራ ስምምነት እንደሚፈረም የአረብ ታይምስ ዘገባ አመላክቷል።

ከስምምነቱ በኋላ በኢትዮጵያ የሚገኙ 600 የሚሆኑ የሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሰው ኃይል በማቅረብ እንደሚሰሩ የተነገረ ሲሆን፤ ሰራተኞች ቢያንስ ብቃቱ ከተረጋገጠ ተቋም የ3 ወር ስልጠና መውሰድ አለባቸው ተብሏል

ኩዌት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቤት ሰራተኞች የምታገኘው ከፊሊፒንስ ሲሆን፤ በኹለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ አገሪቱ የሰራተኛ እጥረት በማጋጠሙ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ማቀዷን ነው ዘገባው ያመላከተው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌት መንግሥት ጋር በተስማሙት መሰረት፤ አንድ ሰራተኛ በወር 90 ኩዌት ዲናር (300 ዶላር) ይከፈለዋል የተባለ ሲሆን፤ ይህም በወቅታዊው የምንዛሬ ተመን ወደ 16 ሺሕ የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ይሆናል። ወደ ፊትም ወርሃዊ ክፍያዉ እስከ 500 ዶላር ከፍ ሊል እንደሚችልም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ኩዌትን ጨምሮ ከቤሩት፣ ከእስያ እና አውሮፓ አገራ ጋር የስምምነት ሥራዎች እንደተጀመሩ መግለጹ
ይታወሳል።

More info

t.me/KuluMedia