Get Mystery Box with random crypto!

በሞታችን የሚሠረጉ ነቢዩ፡- “ እንኳን እንኳ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ” በማለት | የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

በሞታችን የሚሠረጉ
ነቢዩ፡- “ እንኳን እንኳ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ” በማለት ይጸልያል (መዝ. 69÷3)፡፡
ክፉዎች ደስታቸውን የመሠረቱ

ት በሚጠሉት ሰው ውድቀት ላይ ነው፡፡ ደስታቸው መንፈሳዊ ሳይሆን ሰይጣናዊ ነው፡፡ ሠርጋቸውን የሚያደርጉት ሞታችን ላይ ነው፡፡ ወድቀን ካላዩ ደስታ የላቸውም፡፡ የእኛን መርዶ ለመስማት ጆሮዎቻቸው የነቁ ናቸው፡፡ ታዲያ ውርደታችንን ለሚናፍቁ ትልቁ መፍትሔ ከሚያዋርድ ግብር ተጠብቆ መኖር ነው፡፡ እንድንታመም ክፉ ለሚናገሩን አለመታመም መፍትሔው ነው፡፡ ካልታመምን መልሰው ይታመማሉ፡፡ በእውነት መረጃ አለኝ የሚሉ ነገር ግን መርጃ አለኝ ብለው መናገር የማይችሉ ስንት አሳዛኞች አሉ፡፡ ነቢዩ ከእነዚህ እንዲጠብቀው ጸለየ፡፡

ነቢዩ በመቀጠል፡- ‹‹የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስም ይበላቸው፤ ማዳንህን የሚወደዱ ሁልጊዜ፡- እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ›› ይላል (መዝ. 69÷4)፡፡ ነቢዩ እውነተኛ ወዳጆቹ የእግዚአብሔር ወዳጆች እንደሆኑ ያምናል፡፡ የእኛ ወዳጆች የእግዚአብሔር ወዳጆች ላይሆኑ ይችላሉ፤ የእግዚአብሔር ወዳጆች ግን የእኛ ወዳጆች ናቸው፡፡ የእኛ ወዳጆች ቀን ዐይተው፣ መሐላቸውን አፍርሰው ሊለወጡ ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ወዳጆች ግን ፍቅራቸው በዘመናት ያው ነው፡፡ የፍቅራቸው መሠረቱ እውነት እንጂ ሁኔታ አይደለም፡፡ ነቢዩ ስለ መልካሞች ሲጸልይ፣ በእግዚአብሔር ፊትም መልካሙን ሲመኝላቸው እናያለን፡፡

እኛ ስለ መልካሞች መጸለይ የሚያስፈልግ አይመስለንም፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው እንዲጸኑ ጸጋን መለመን ተገቢ ነው፡፡ ከእነርሱ ያነስን ደካሞች መሆናችንን ብናምን እንኳ መጸለይ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ጸሎትን የሚመልሰው አንዱና ብርቱው እግዚአብሔር ነውና፡፡ በመልካሞች ፊት ስለ መልካምነታቸው ውዳሴ ከማቅረብ፣ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እነርሱ መጸለይ እውነተኛነት ነው፡፡

እውነተኛ ደስታ ያለው እግዚአብሔርን በመሻት ውስጥ ነው፡፡ የዓለም መሻት እንቅልፍ የሚነሣ እንጂ የሚያሳርፍ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ግን ሲሹት እንኳ ያረካል፡፡ የእግዚአብሔርን ትድግና ብቻ የሚጠባበቁም ታላቅነቱን እንደሚያዩ ነቢዩ ተናግሯል፡፡ እኛስ የምንሻው ምንድነው? መዳንን የምንናፍቀውስ ከርእዮተ ዓለሞች ወይስ ከአዋቂዎች ነው? እግዚአብሔር ታላቅ ነው ብለን በሥራው ለመዘመር ተስፋችን እርሱ ሊሆን ይገባዋል፡፡

እግዚአብሔር ለማዳን ያያል!! ሰዎች ለትዝብት፣ እግዚአብሔር ግን ለመሸፈን ያያል፡፡ ሰዎች ያዩትን ለማሳየት፣ እግዚአብሔር ግን በጉድለታችን ላይ ሙላቱን ለመግለጥ ያያል! ለትልልቅ ሰዎች ችግራችንን ለማስረዳት፣ የጠቢባንን እርዳታ ለማግኘት ብዙ ዘመን ተገልጠናል፡፡ በነጩ የጽድቅ ሸማ ለሚሰውረው ጌታ ግን ዛሬ እንገለጥ፡፡ ከነቢዩ ጋር እንዲህ እያልን እንጸልይ፡-

‹‹እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፤ አቤቱ÷ እርዳኝ፤
ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ፤ አቤቱ÷ አትዘግይ››
(መዝ. 69÷5)፡፡

እንኳን የምስራች ነጋሪ ለሆነው አብሳሪው ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።

@Ortodox_27